Muhamed Authorized Public Accountant

Muhamed Authorized  Public Accountant

Share

የሂሳብ ስራ አገልግሎት
IFRS ስልጠና እና ማማከርይደውሉ፡፡
? Accounting Service
Tax accounting service
maintain Internal control Structure

04/04/2026

Things grow when you start !!

13/01/2026

Cash flow

01/12/2025
15/11/2025

ለንግዱ ማህበረሰብ እና አዲስ ንግድ ፍቃድ ለማውጣት ለምትፈልጉ ዜጎች ። በቀጣይ የምሰጠው መረጃ ገንዘብ ከፍላችሁ የማታገኙን ስለሆነ በደንብ ከታዩት መልካም ነው።

ትላንት አንድ የአ.አ ገቢዎች ቢሮ የታዘብኩት ነገር ቢኖር ከ5እና 6 ያለነሱ ግብር ከፋዮች በአጥር ጥግ እየሆኑ ለብቻ ለብቻ እንባ አውጥተው ሲያለቅሱ ተመልክቼ ምክንያታቸውን ስጠይቅ የመጣብኝ ግብር በፍፁም ልከፍለው አልችልም ቤተሰቤ ሊበተን ነው አንዴት መክፈል እችላለሁ ? እንዴት ንግድ ፍቃድ መመለስ እችላለሁ የሚሉ ድምፆችን አስምተውኛል። በእውነቱ ዜጎች እንደዚህ ሲጨነቁ መመልከት እጅጉን አሳሳቢ ነው።

የእኔ ምክር

የሂሳብ መዝገብ ለምትይዙ ነጋዴዎች።

1 የባንክ አካወታችሁ ላይ በፍፁም ከሽያጭ ውጭ ምንም ገንዘብ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለባችሁ ተሳስቶ እንኳን ሰው ብር ቢልክላችሁ ከባድ ነው ነው የብሩን ምንጭ ትጠያቃላችሁ + ለተገዛው እቃ በሙሉ ከሂሳባችሁ መከፈል አለበት።

ለምሳሌ በባንክ አካውንታችሁ 100,000 ብር ቢገባ ገቢዎች 100,000*35% =35,000 ብር ግብር ይጠይቃሉ ።

2 ሽያጫችሁ በትንሹ 21% ትርፍ ሊኖረው ይገባል ።

ለምሳሌ አንድን ዕቃ በ100 ገዝታችሁ ከሆነ በትንሹ በ121 ብር መሸጥ ይኖርባችኋል ይህ ሳይሆን ቀርቶ በ100 ብር ገዝታችሁ በ110 ብር ብትሸጡ ገቢዎች 121_110=10*35% 3.5 እያንዳንዱ ሽያጭ ላይ ግብር ይጠይቃል ።

3 ብድር ከሌላ ሰው ስትበደሩ በውልና ማስረጃ መሆን አለበት አንድ ሰው በሰፈር ውል 1ሚሊዮን ብር ቢበደር መንግስት 1,000,000*35%=350,000 ብር ግብር ይጠይቃል ።

4 ዓመታዊ ጠቅላላ ሽያጭ ላይ የሚጣለው ትንሹ ግብር 2.5% መሆኑን አውቃችሁ እራሳችሁን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መክሰር ያስቀጣል ።

ለምሳሌ ድርጅታችሁ አመታዊ ሽያጭ 2ሚሊዮን ሆኖ 100,000 ብር ቢከስር 2,000,000*2.5%=50,000 ብር ግብር ትከፍላለችሁ።

5 ለንግዱ ከአወጣችሁት አስተዳደር ወጪዎች ውስጥ ኦዲተሮች 35% ውድቅ ማድረግ ይችላሉ ።

ለምሳሌ በአመት ውስጥ ለንግዱ የወጣው ወጪ 100,000 ቢሆን ምንም እንኳን ደረሰኝ ቢኖረውም 35,000 ብሩን ውድቅ በማድረግ 35,000*35%=12,500 ተጨማሪ ግብር መጠየቅ ይችላል ።

6 ከሰው የተበደራችሁት ብድር ቢኖር ለአበዳሪው ግለሰብ ስትከፍሉ በስሙ በባንክ መክፈል ይኖርባችኋል ።
ምሳሌ
አንድ ነጋዴ ከቤተሰቡ ወይም ከወዳጆቹ 1ሚሊዮን ተበድሮ ከሆነ እና በዓመቱ 600,000 ቢከፍል 600,000 በባንክ መሆን አለበት ከአልሆነ ግን በተለያየ ጊዜ በካሽ ቢከፍል ውድቅ ተደርጎ በ600,000*35%=210,000 ብር ግብር ይከፍላል ።

6 አንድ ነጋዴ ከራሱ ሂሳብ ገንዘብ በዓመቱ ማውጣት የሚችለው የትርፉን መጠን ብቻ ነው።

ምሳሌ አንድ ነጋዴ በዚህ ዓመት የተጣራ ተርፍ 400,000 ቢኖራው እና በሂሳቡ ላይ ከሽያጭ የተገኘ ገንዘብ 1,000,000 ቢኖረው አስቻኳይ ነገር ቢያጋጥመው 400,000 ብር ብቻ ማውጣት ይችላል 500,000 ብር ቢያወጣ 500,000_400,000=100,000*35%=35,000 ግብር ይከፍላል ።
7 outstanding inventory =( beginning + total purchase ) _ total sales ከአልሆነ እያንዳንዱን inventory ዝርዝር ማቅረብ ግዴታችሁ ነው።

8 አንዳዴ አልፎ አልፎ Lifo Fifo Average የሚባሉትም ልትጠየቁ ትችላላችሁ ነገር ግን አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ነጋዴዎች Average ስለሚጠቀሙ እረኛው ብዙ አሳሳቢ አይደለም።

Postu ye Eliana Firew new

10/07/2025

ለግብር ከፋዬቻችን በሙሉ
የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀምና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 149/2011 ን ለማሻሻል በወጣው ማሻሻ መመሪያ ቁጥር 188/2017 መሰረት ማንኛውም ነጋዴ የሚጠቀምበት ማንዋል ደረሰኝ ህትመት QR code የተካተተበት እንዲሆን እና ህትመቱም በብርሃንና ሰላም እንደሚካሄድ መገለጹ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የደረሰኝ ህትመቱ በወቅቱ እየደረሰ ባለመሆኑ ነባሩን ደረሰኝ የመጠቀሚያ ጊዜ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙ ይታወቃል፡፡
አሁንም የደረሰኝ ህትመቱ በሚፈለገው ልክ ያልተሰራጨ በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ወደ QR code ደረሰኝ መሸጋገር ስላልተቻለ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ተራዝሞ የነበረውን የነባሩን ህትመት መጠቀሚያ ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም እየተዘጋጀ ያለውን መመሪያ በዚሁ ቻናል እስክናሳውቃችሁ ድረስ ነባሩን የደረሰኝ ህትመት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ወደፊት ለሚኖረው አሰራር በተቋሙ ድህረገፆች የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡

02/07/2025

በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች ንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች የንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ አሉ።

አቶ አህመድ ሺዴ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዳ እየከፈለ የሚገኘው መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ገቢ እያገኘ መምጣቱን ገልጸው፤ ገቢ የማያስገኝ አገልግሎት አክሳሪ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የንብረት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ መደረጉን በማስታወስ፤ በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀመራል ነው ያሉት።

አዲስ መንገዶችን ለመስራት በበቂ ሁኔታ ጥናት ማደረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አህመድ፤ ባለፉት 7 አመታት የልማት ኢ-ፍትሐዊነት ከተነሱባቸው መካከል መንገድ ዋነኛው መሆኑን ነው ያነሱት።

የመንገድ ፕሮጀክቶች እቅድ እና የተያዘላቸው በጀት ተመጋጋቢ እንዳልነበሩ ጠቅሰው፤ ችግሩን ለመፍታት በቂ ጥናት ተደርጎ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል፡፡

ለመንገድ የተመደበው በጀት ከሁሉም ሴክተሮች እንደሚበልጥም ነው ያነሱት አቶ አህመድ ሺዴ፡፡

የመልሶ ማቋቋምን በተመለከተም መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

የካሳ ክፍያ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እያስከተለ በመሆኑ ለካሳ ክፍያ በሚል የሚደረጉ ያልተገቡ እንቅስቃሴዎች ላይ ክልሎች በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

በዚህም የመሰረተ ልማት አስፈላጊነት ላይ ህዝቡ ግንዛቤ እንዲጨብት በማድረግ መንግስት ያለበትን የወጪ ጫና መቀነስ ያስፈልጋል ነው ያሉት ፡፡

በጀቱ ድህነትን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እና የማክሮ ኢኮኖሚውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዝም አስገንዝበዋል።

(አቤል ንዋይ - ኤፍ ኤም ሲ)

Want your business to be the top-listed Accountant in Bahr Dar?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Bahirdar
Bahr Dar