በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት "በከተማው የሚገኙትን ግብር ከፋዮች ባህርያት
1ኛ ለታክስ ህግ ተገዢ የሆኑ
2ኛ ለታክስ ህግ ተገዢ መሆን ፈልገው የማይሳካላቸው
3ኛ ለታክስ ህግ ተገዢ የመሆን ፍላጎት የሌላቸው በሚል በ3 ክፍሎች በመመደብ
1. ለታክስ ህግ ተገዢ የሆኑትን በማበረታታትና አገልግሎት ቅድሚያ በመስጠት፣
2. ለታክስ ህግ ተገዢ መሆን ፈልገው የማይሳካላቸውን ድጋፍ፣ስልጠና እና ምክር በመስጠት ወደ ህግ ተገዢነት እንዲመጡ ማድረግ
3. ለታክስ ህግ ተገዢ የመሆን ፍላጎት የሌላቸውን ወደ ታክስ መረቡ በማስገባት ጥብቅ ቁጥጥር እና ህጋዊ እርምጃ በመውስድ ለታክስ ህግ ተገዢ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ በሰፊው እየሰራ እንደሆነ" የሰመራ ሎግያ ከተማ ገቢ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ Mohammed Awel ገልጸዋል።
Via Afar Mass Media Agency
Samara-Logiyi Ma/Xi/Culenti k/Buxa የሠመራ - ሎግያ ከተ/መስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት
Culenti Baxok Diiror Lafa!!
13/01/2026
የሰመራ ሎግያ ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ከ264 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ ።
ሰመራ ፣ ጥር 5፣ 2018 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት በበጀት አመቱ ባለፉት 6 ወራት ከ264 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል ።
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ አወል የበጀት አመት የስድስት ወራት የገቢ አሰባሰብ ሂደትን አስመልክተው ለአፋር ቴሌቪዥን መግለጫ ሰተዋል
የፅ/ቤት ሀላፊው በመግለጫቸውም በበጀት አመቱ በስድስት ወራት 284 ሚሊዮን 639 ሺህ 913 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ264 ሚሊዮን 652 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረው ይህም 93% ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል
ሀላፊው አክለውም ገቢው ቀጥተኛ፤ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች የተሰበሰበ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል
በመጨረሻም አቶ መሀመድ አወል በቀሩት ግዜያት እቅዱን ከግብ ለማድረስ ፅ/ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆኑን በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
Via Afar Mass Media Agency
18/10/2025
Sa/Lo/Ma/Xi /Cu/Ku/Buxak 2017 Baajet sanatak alfenti Barnamij asaakih ayro qaxmeqe gurral yumurruqe.
*****************************************
Qafar Ag/Ra/Do/Samara-Logiyi Ma/Xi/Culenti K/Buxa.
****************************************
Barnaamijil meqe Taamah abnisso tuybulleeh tan taama abeyniitih gaddi gacsaa kee acwah sumaqta tonto cowwe . Culenti K/Buxah Saqalah yan Massakaxxale Mocammad Awel Amqaso 2017 baajet sanat 380 Millioni (100%) daga yakke culenta gaaboysak duddale taamah abnisdoh xalu aynallayuk Neemeete iyye.
Saqal qagitaakl, ciggiilah yan 2018 baajet sanat qidaddo akak ractah tan culenti gaaboyso duddaay. emnetluk abnak faxximta. Iyyah yan maftacak tan farmooy tat ruse. Ma/da/ Qi/ bisoh haynuh duddale culenti gaaboobam faxximtam warsen.
*********************************************
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የመዝጊያ ፕሮግራም በድምቀት አከናወነ!
********************************************
በአፋር ብ/ክ/መንግሥት የሰመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት
*********************************************
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የመዝጊያ ፕሮግራም በድምቀት አከናወነ!በፕሮግራሙ ላይ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላሳዩ ሰራተኞች ምስጋናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ አወል አምአሶ፣ "የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ከ380 ሚሊዮን (100%) በላይ የሆነ ገቢ በመሰብሰብ ትልቅ ስኬት አስመዝግበናል" ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም "ለቀጣዩ ለ2018 በጀት ዓመት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ ጠንክረን በታማኝነት መስራት አለብን" የሚል ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የከተማ አስተዳደሩን ልማት ለማስቀጠል ገቢን በታማኝነትና በብቃት መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን አጽንዖት ተሰጥቷል።
06/09/2025
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በግብር እና ታክስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ።
ሠመራ ፣ ጳጉሜ 1/2017 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ በሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ግብር ከፋዮች በግብር እና ታክስ ህግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ በሎግያ ከተማ ሰጥቷል ።
በእለቱም የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/17 የተመለከተ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አወል አብዱ ባደጉረት ንግግር የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
በመሆኑም ለትግበራው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ገንቢ ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ አብዱ ሙሳ እንዳሉት በከተማዋ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቅባቸውን የገቢ ግብር ግዴታ በወቅቱ በመክፈል ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ መሀመድ አወል አዲስ የተሻሻለውን የገቢ ግብር አዋጅን የተመለከተ ገንቢ ውይይት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ማድረጋቸውን ተናግዋል።
በጣቀይ ግብር ከፋዩ ያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ፅ/ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም አመላክተዋል ተናግረዋል።
በመጨረሻም የንግዱ ማህበረሰብ እንደተናገሩት አመታዊ የገቢ ግብር ጥናትን መሰረት ተደርገው ተግባራዊ እንዲደረግ ሀሳባቸውን ያነሱ ሲሆን ለተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ትግበራ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል ።
Via Afar Mass Media Agency
06/09/2025
Culenti biiro samara-logyi magaalah xiinissol culenti uguugusih taddiira abak maacisse
**********************************
Paagumek 1/2017 I.L.L
Culenti-Biiro
Qafar rakaakayak culenti biiro culenti maglableelâ luk cattiimak samara-logyi magaalah xiinissoh gubat raqtah tan kabxaabeyniitih qusbah yan culenti qisoh kuktay qusbannal missos kak yekke kee kalah tan baxaabaxsale qisô madqah dacayri wagittaamal baarle walal kee tû ced aydakaakan gexsen.
Culenti uguugusuy yekkel rakaakayak culenti biirok naharsi saqal massakaxxale cajji Awwal Qabdu Awwalaay, Qisoh Oxiit kee Madqa Dacayrih langik C/Saqaal Masakaaxxa le Jaamal Qali, samara-logyi magaalah xiinissoh saqal gifta Qabdu Muusaay, samara-logyi magaalah xiinissok culenti kutbeh buxah saqal gifta Macammad Awwal Kee Logyi makaaftah saqal gifta Nasri Macammad elle geytimak gudgud qembisen.
Tama aracal yabti fakkenta abeh yan massakaxxale Awwal Qabdu Awwal culenta maleh tekke baaxo matanaay, culenti inki baaxoh dadalak rakiibo kinnuuk qisô madqa dacrisak baaxô konnabnah abna macalal siita catak ittaluk bisoh innam faxxintam qaddoyse. Qagitaak, abeh yan yaabal tekkeh tan maysaasa kabxaabeyniitil akkuk sugeh yan gibdaabina kee qisô gaaboysol yanih yan qadli sinna ankuslem aamanuk tekke maysaasa kinnim yescesse. Kalah kaadu gudgudul geytimeh yan samara-logyi magaalah xiinissoh saqal gafta Qabdu Muusa tanim siitalluuk aaxagauk kabxaabeynit sinni dirkik tawaquh dudda keenik gablusaanam faxxintam yescesse.
Ellacabol qarih saami acayuk kabxaabeynit le gatuk ugutteh tan esseroorah radditte gacisak gudgud meqe gurral yumurruqe.
Via Qafar Rakaakayih Doolatak Culenti Biiro አ/ብ/ክ/መ/ገቢዎች ቢሮ
02/07/2025
የ2017 ግብር መክፈያ ጊዜ ደረሰ
የሰመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት እንኳን ለ2017 የግብር መክፈያ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ
-የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የመክፈያ ወቅት ከሐምሌ 01 እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም
-የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 01 እስከ ጳጉሜ 05(06)/2017 ዓ.ም
-የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 01 እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ድረስ መሆኑን እያስታወስን ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በታማኝነት እና በወቅቱ በመክፈል ከአላስፈላጊ ቅጣት ፣ ወለድና መጨናነቅ እንዳትዳረጉ ከወዲሁ እናሳስባለን።
-ግብር በታማኝነት እና በወቅቱ መክፈል መሰልጠን ነው!
-ግብር ለሀገር ክብር
-ግብር ለሀገር ብልፅግና
02/07/2025
2017 meeri meklah uddur gufeh
Semera_logya Magaalah Xiinissok Culenti Kutbeh Buxa Sanat 2017 qiso meklah Uddur meqe gurral sin Sugseh Nee Sugsem Axcuk.
- "C" footimak qiso Meklah uddur ximolik 01 ilaa ximolik 30/2017ILL meklaanam
- "B" footimak Meklah uddur Diteli alsak 01 ilaa Pagume 05(06)/2017 ILL.
- "A" footimak qiso Mekla waktih meklaanam Juulay alsak 01 ilaa Kaxa garablu 30/2018 ILL. meklaanam
Nanu qiso mekla mara ken qiso qaadiino kee waktil meklaanam faxxiime sinni digaalaay, riba kee udurra soolisaanam Duma Mekeltanam Sin kassisna.
Qiso waktil meklaanam Dadadalak qaada!
-Qiso Baaxoh kunnabnah!
-Samara-Logyi Magaalah Xiinisok Culenti K/Buxa
04/06/2025
16/05/2025
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት በያዝነው በጀት አመት በ10 ወር ከ330 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ አወል አምአሶ ገለፁ።
******************************************
የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት በያዝነው በጀት አመት 380,358,595 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ በ10 ወር 330,374,041.96 መሰብሰቡን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ አወል አምአሶ ገለፁ።
ይህም አፈፃፀም ከባለፈው በጀት አመት (2016) ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 155,336,489.5 (89%) እድገት እንዳሳየ ገልፀው የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ጽህፈት ቤቱ ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ ጋር በመቀናጀት ለማህበረሰቡ ፣ ለግብር ከፋዮች እና ለባደርሻ አካላት ስለ ታክስ ምንነት እና በታክስ ህግ ተገዥነት ዙሪያ የተካሄዱ ውይይቶች፣ ስልጠናዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጫዎች የታክስ አሰባበሱ ላይ ትልቅ ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉን አስታውሰዋል። የጽህፈት ቤት ኃላፊው አክለውም የገቢ ጉዳይ የገቢ መስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ማህበረሰብ ክፍል መሆኑን ገልፀው በመጨረሻም የታክስ ፍትኃዊነት እንዲረጋገጥ የደረጃ "ሀ" እና ደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ለፈፀሙት ግብይት እና ለሰጡት አገልግሎት ደረሰኝ እንዲቆርጡ፤ ማህበረሰቡም ማንኛውንም ግብይትና አገልግሎት ሲያገኝ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህሉን እንዲያዳብር የሰመራ ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ አወል አምአሶ ጥሪ አቅርበዋል።
ግንቦት 2017
ሰመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት
ሰመራ
16/05/2025
Semera Logya Magaalah Xiinissok Culenti Kutbeh Buxa Awayih Uddur Mizaaniyyat Liggidal 330 Miliyoonih Birriik Daga Gaaboyseenim Kutbeh Buxah Saqal Giffta Macammad Awol Amqasso Qaddoose.
06/9/2017 ILL Samara
***************************
Semera Logya Magaalah Xiinissok Culenti Kutbeh Buxa Awayih Uddur Mizaaniyyat Liggidal 330 Miliyoonih Birriik Daga Takke Lakqo Gaaboyseenim Tama Kutbeh Buxah Saqal Ato Macammad Awol Amasso Qaddoose. Ta Xayyos Taturte Mizaaniyyat Liggidak Inki Alsaak 87% Osotina Geytimam K/Buxah Saqal Yescese .
Kutbeh buxa, Rakaakayak Culenti biirot ,cattiimak Magalah Ayuntaay, qiso mekla mara kee wagsiisah tan xagaritteh qiso gino kee qiso madqooqi yassakaxxeenim, qiso gaaboysoh raddil kaxxa milaagu bahte kutbeh buxa kinnim Qadoyse.
Ellecaboh, Culenti Kutbeh Buxah Saqal Macammad Awol, "A" Footima Kee "B" Footima Qiso Meklaanam, Qiso Qadliino Akah Yaysiisen Innah Abak Geytiman kee Taama Ayfaafayitteh yoofenta Akah Yayyaaqen Innah Kassiise.
ayyunti yoofenta esseraanam Fayxit Taadem Hinay Diirki Kinimik Amakaquk Ayunti Sini Diirkik Yawqem Faxintaa Axcuuk K/Buxah Saqal Macammad Awwal Amqaso ayyunti kassiiseh Farmo Tatruse.
******************************
Laqiin /06/2017ILL SAMARA
Semera-logya Magaalah Xiinissok
Culenti Kutbeh Buxa
29/04/2025
Maysaaxag
Ahak Gubal Migaaq Kak Yan Qiso Mekleenitik inkih Birhaan Kee salaam Maysaaraq Amriseenih tanin yoofenta Bahneemih Tagaah kabxa leh Yan Num Hinamay Missoynanik Ganuun awlaaytino Leh yan Dagaar kee Teelemo roksat Koopi Kee Mahtab Luk Rakaakayak Culenti Biiro xayyowak Yoofenta Beytanam Sin Naysixxige.Tohuk lakal NiQiso Mekleenitik yoofenta Dagna Sinik telekatekek Birhaan Kee Salaam Maysaaqara Yoofenta Atbiiqiyi Uddur Beeyam kinnuk Taamal adafa sinik Boodamak Qagittak Yoofentah Essero Xayyyosanam Masakaxxa luk Sin Naysixxige.
ማስታወቂያ
ከዝህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረው ግብር ከፋይዎቻችን ለብርሃንና ሰላም የታዘዘው ደረሰኝ ስለመጣ ባለቤት ወይም ህገዊ ውክልና እንድሁም ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማህተም ይዛችሁ በመምጣት ደረሰኝ ውስን ከሆነ ብርሃን እና ሰላም ጋር ደረሰኝ ለማተም ብዙ ጊዜ ስለሚወስድ ስራችሁ ለይ እክል እንዳይፈጠር ደግማችሁ እንድታዙ ለማሳሰብ እንወዳለን።
/Ag/Ra/Do/Culenti Birro
20/02/2025
"ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራርን እውን ማድረግ ለተጣጣመ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ግንባታ ውጤታማነት አይተኬ ሚና አለው"
ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚንስትር )
የካቲት 13/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የክልልና የከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን በመገኘት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የልምድ ልውውጥና የጉብኝት መርሐግብር እያካሄዱ ነው፡፡
በእለቱ የገቢዎች ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የልምድ ልውውጥ መድረኩ ከገቢ አሰባሰብ አኳያ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች ተቋማት ተሞክሮ የሚለዋወጡበትና ለጋራ ስራ መግባባት የሚፈጥሩበት ነው ብለዋል።
ክልሎች የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ ታክስ መሰብሰብ የሀገር የጀርባ አጥንት የሆነውን የፍይናንስ አቅርቦት በማሳደግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ዋነኛ መሳሪያ ነው ብለዋል::
በተጨማሪም በራስ አቅም የሀገርን ሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከለውጡ በኋላ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው የገቢና ወጪ የንግድ እንቅስቃሴን የተሳለጠ ለማድረግ የዲጂታል የታክስ ስርዓትን ማፋጠን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የገቢ ሰብሳቢ ተቋማትን ማጠናከር፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ማዘመን ከመቼውም ጊዜ በላይ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ከዚህ አኳያ የልምድ ልውውጥ መድረኩ ኢትዮጵያን ለማልማትና የገቢ እቅዶቻችንን ለማሳካት ስራችንን የምናጠናክርበትና አዳዲስ ስልቶችን የምንቀይስበት መሆን አለበት ብለዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም ለልምድ ልውውጥ የተገኙት አመራሮች የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ ቤትን ጨምሮ በጉሙሩክ ኮሚሽን የጭነት ደህንነት መከታተያና መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ክፍል፣ የአይቲ ማዕከላትን እንዲሁም የከፍተኛ ግብር ከፍዮች ቅ/ጽ/ቤትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የልምድ ልውውጡ በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን በዚሁ ቀን ቃሊቲ ጉሙሩክ፣ ሞጆ ጉሙሩክ እና ሌሎች ቅ/ጽ/ቤቶችን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል፡፡
በሶስና መልኬ
ፎቶ፦ እስከዓለም ሰፊው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Website
Address
Logya
7240